በ40 ሚሊዬን ዶላር የተገነባው የኬብል ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ

81

ሚያዝያ 24/2011 ኩባንያው በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ በ40 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን የኬብል ማምረቻ ፋብሪካ ዛሬ አስመረቀ 

ዩሮ ኬብል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ በ40 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባውን የኤሌክትሮኒክ ማስተላለፊያ ኬብል ማምረቻ ፋብሪካ ዛሬ አስመርቋል።

በምርቃት ስነ-ስረዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

ድርጅቱን የመሰረቱት የኢትዮጵያና የቱርክ ባለሃብቶች ሲሆኑ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በኬብል ምርት ላይ ሲሰሩ ቆይተዋል።

የፋብሪካው መከፈት የድርጅቱን የምርት መጠን በሶስት እጥፍ እንደሚያሳድገውም ተገልጿል።

ድርጅቱ ስራ ሲጀምር ዝቅተኛ የቮልቴጅ መጠን ማስተላለፍ የሚችሉ ኬብሎችን ብቻ ሲያመርት እንደነበር ተገልጾ በአሁኑ ወቅት ግን በመሬት ውስጥ የሚቀበሩና አደጋን መቋቋም የሚችሉ፣ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ የዳታና የሳተላይት ኬብሎችን ማምረት ወደ ሚችልበት ደረጃ ተሸጋግሯል።

ከአስር አመት በፊት ድርጅቱ በ55 ሚሊዮን ብር ካፒታልና በ30 ሰራተኞች ተቋቁሞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለ200 ሰዎች የስራ እድል የፈጠረና ከ680 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል እንዳፈራም ተነግሯል።   

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም