የምህረት አሰጣጥ ረቂቅ አዋጁ ለተጨማሪ እይታ ተላለፈ

120
አዲስ አበባ ግንቦት 28/2010 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምህረት አሰጣጥ እና የሰራተኛ ቅጥር ስምምነት ረቂቅ አዋጆችን ለተጨማሪ እይታ ለቋሚ ኮሚቴዎች መራ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሔደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባው  የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የምሕረት አሰጣጥ እና አፈጻጸም ሥነ-ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል። በዚህም ምሕረት የሚሰጥበትን ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን መርምሮ ለሕግና ፍትሕ ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መርቷል። በተጨማሪም በኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ መንግስት መካከል የተደረገውን የቤት ሰራተኞች ቅጥር ስምምነት ለማድደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለውጭ ጉዳዩችና ለማሕበራዊ ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ አስተላልፏል። ኢትዮጵያና ሳውዲ አረቢያ ባሳለፍነው ዓመት የሰራተኞች ቅጥር ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። ስምምነቱ በቤት ሠራተኞች ምልመላ ትብብሩን በማሳደግ የሁለቱን አገሮች ፍላጎት ባገናዘበና ሉዓላዊነታታውን ባከበረ መልኩ የሰራተኛውንና የአሰሪውን መብቶችን ለማስጠበቅ ዓላማ ያለው መሆኑም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም