በህንድ በአውሎ ንፋስ ሳቢያ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እየለቀቁ ነው

84

ሚያዚያ 24/2011በህንድ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ በተነሳ አውሎ ንፋስ ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መኖሪያቸውን ለቀው እየወጡ ነው፡፡

ፋኒ ተብሎ በሚጠራው በዚሁ አውሎ ንፋስ ሳቢያ ከህንድ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻዎች ወደ ኦሪሳ ግዛት እየተጠጋ በመምጣቱ የመሬት መንሸራተት ያስከትላል በሚል ስጋት ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ አስገድዷል፡፡

በሰዓት 200 ኪሎ ሜትር እየፈጠነ ያለው ይኸው አውሎንፋስ በነዋሪው ላይ ሊያደርሰው የሚችለውን አደጋ ለመታደግ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በአካባቢው የሚገኙ ሁለት ወደቦች ስራ እንዲያቆሙ ማድረጋቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አካባቢውን ለቀው ወደሌላ አካባቢ እንዲሰፍሩ እያደረጉ ነው፡፡

ከዚህ አደጋ ጋር ተያይዞ 800 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ከባህር ዳርቻው እንዲወጡ ሄደቱ የተጀመረ ሲሆን አንድ መቶ ሺህ የሚጠጉ ነዋሪዎች አውሎንፋሱ ይጠነክራል ከተባለበት ከኦሪሳ ግዛት ይወጣሉ ተብሏል ፡፡

በዚሁ ግዛት 858 አመት እድሜ ያስቆጠረ የአምልኮ ስፍራ ህንፃ ጉዳት ይደርስበታል የሚል ስጋት በባለስልጣናቱ በኩል መኖሩን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

በግዛቲቱ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች መዘጋታቸውንም ነው ዘገባው የጠቆመው ፡፡

ባለፉት 30 አመታት ለአራት ያህል ጊዜ የሃገሪቱ ምስራቃዊ ዳርቻ በአውሎ ንፋስ መመታቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም