የኡጋንዳ 13 የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የተወሰኑ ጋዜጠኞቻቸውን ከስራ እንዲያግዱ ትዕዛዝ ተሰጣቸው

68

ሚያዚያ 24/2011የኡጋንዳ ኮሚዩኒኬሽንስ ኮሚሽን የተሰኘው ተቆጣጣሪ ተቋም ለጣቢያዎቹ ከጋዜጠኞች በተጨማሪ የዜናና ፕሮግራም ሃላፊዎችንም እንዲያግዱ ነው ትዕዛዝ ያስተላለፈው።

ኮሚሽኑ መረጃን አዛብቶ በማሰራጨት እንዲሁም ጽንፈኝነትንና ስርዓት አልበኝነትን የሚቀሰቅሱ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚያደርግ ስራ ሰርተዋል በሚልም ወንጅሏቸዋል።

ተቋሙ ኤን ቢ ኤስ ቴሌቪዥን፣ ቡኬዴ ቴቪ፣ ኤንቲቪ፣ ሲቢኤስ ኤፍ ኤም፣ እና ካፒታልፍ ኤምን ጨምሮ ለ13 የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የእርምጃ መልዕክት ልኳል።

ለጣቢያዎቹ በደረሳቸው መልዕክት በዝርዝር ምን ዓይነት ጥፋት እንደፈጸሙ የሚያሳይ ጉዳይ (ኬዝ) አልተጠቀሰላቸውም ተብሏል።

በሶስት ቀናት ውስጥም፣ አዘጋጆችን፣ የዜና እና የፕሮግራም ሃላፊዎችን እንዲያግዱ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ነው የተነገረው።

ጣቢያዎቹ በቀጥታ ስርጭት፣ በሰበር ዜና፣ በመፅሄት ፕሮግራሞችና በዋና የዜና ሰዓታት የብሮድካስቲንግ ዝቅተኛ መስፈርትን የሚጥሱ ይዘቶች በማሰራጨታቸው እርምጃው እንደተወሰደባቸው ኮሚሽኑ ገልጿል።

ምንጭ፦ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም