በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው

585

ባህርዳር፣ ጎንደር ፣ ደብረማርቆስ ሚያዝያ 24  2011 በአማራ ክልል በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ደብረ ማርቆስን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች የዜጎች መሞትና መፈናቀል ይቁም በሚል ሰላማዊ ሰልፎች እየተደረጉ ነው፡፡

ሰልፎቹ በወጣቶች አስተባባሪነት እየተከናወኑ ሲሆን የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ቅሬታቸውን እያቀረቡ ይገኛል፡፡

እየተሰሙ ካሉት መፈክሮች መካከልም በመተከልና አካባቢው እየደረሰ ያላው የአማራ ሞትና መፈናቀል በአስቸኳይ ይቁም፣አሻጥረኞችን እንጂ ሁለም ኢትዮጵያዊ ወንድማችን ነው፡፡

በአማራ ምድር የሚኖሩ የየትኛውም ብሄር ተወላጆች ላይ ጥቃት የሚፈፅም የአማራ ዋነኛ ጠላት ነው የሚሉና ሌሎችም መልዕክቶች ተንጸባርቀዋል።

ሰላማዊ ሰልፉ ከባህር ዳር ፣ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስ በተጨማሪ በመራዊ፣ ደብረታቦርና በሌሎች ከተሞች በሰላማዊ መንገድ እየተከናወኑ ይገኛሉ።