የሚዲያ ነፃነት ያመጣውን ፈተና ለማለፍ መንግስትና ጋዜጠኞች ለአገር ህልውና መስራት አለባቸው-የዘርፉ ምሁራን

88

አዲስ አበባ ሚያዝያ 23/2011 የሚዲያ ነፃነት ያመጣውን ፈተና ለማለፍ መንግስትና ጋዜጠኞች ከራስ ፍላጎት አልፈው ለአገር ህልውና መስራት እንዳለባቸው የዘርፉ ምሁራን ተናገሩ።

ነፃ ሚዲያ ማለት የሚደገፍ ብቻ ሳይሆን የሚወቀስም እንደሆነና ችግሮች እንዳለበትም ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ለ26ኛ ጊዜ የተከበረውን “የፕሬስ ነፃነት ቀንን” መነሻ በማድረግ በተዘጋጀው መድረክ የረጅም ጊዜ ልምድና ተሞክሮ ያላቸው ታዋቂ ግለሰቦችና የዩኒቨርስቲ መምህራን እንዲሁም የአበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተሳትፈው ግብዓት ተገኝቶበታል።

ውይይቱ የፕሬስ ነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት ለማስቻል ነው ያሉት የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ኃላፊ ዶክተር ጌታቸው ድንቁ መንግስት ከሚዲያ አካላትና ከዘርፉ ምሁራን ልምድና ግብዓት የሚቀስምበት እንደሆነም ገልፀዋል። 

በጋዜጠኝነት ሙያዊ እሳቤ ላይ በመመካከር ተመሳሳይ አቋም ላይ ለመድረስ ነውም ብለዋል። አያይዘውም የሚዲያ ተቋማት የጋዜጠኝነት ሙያን በማስቀደም ለህብረተሰቡ መረጃ ተደራሽነትና መጣር እንዳለባቸው ግብዓት የሚያገኙበት በመሆኑም መድረኩ ወሳኝ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ የነበሩት ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ እንዳሉት ዘንድሮ መንግስት ለሚዲያ ነፃነት በመስጠቱ ወደፈተና የገባበትና ፈተናውን ማለፍ በጥረት ላይ ያለበትና፤ የሚዲያው ተቋማትም ደግሞ ከተቋቋሙበት አንፃር የተፈተኑበት ነው ብለዋል።

በአገሪቱ የሚዲያ ካውንስል እንዲቋቋም ጉልህ ሚና የተጫወቱና የአርት ቴሌቪዥን መስራች አቶ አማረ አረጋዊም ኢትዮጵያ ምንም እንኳን የፕሬስ ነፃነትን በህገ-መንግስታቸው ካካተቱ የአፍሪካ አገራት ውስጥ አንዷ ቢያደርጋትም በተግባር ላይ የማዋል ድክመት ይታይበታል ብለዋል።

ለዚህም መንግስት፣ የሚዲያ አካላት፣ ተቃዋሚዎች እንዲሁም የውጭ ጣልቃ ገብነት ተወቃሾች መሆናቸውን በዝርዝር አንስተዋል። አቶ አማረ የአገሪቱ ሚዲያ የመረጃ ተደራሽነቱ ለግልና ለመንግስት ወጥነት አለመኖር፣ የበጀት ችግር፣ የሚዲያዎች ጎራና ለሐቅ ያለመቆም እንዲሁም የጋዜጠኝነት ሙያ በውል ያለመለየት ችግሮች ተደቅነውበታልም ብለዋል።

በመሆኑም የሀገር ህልውና የቆመው በህዝቡ ጨዋነት እንጂ በሚዲያ ብቃት እንዳልሆነ ገልፀዋል።

የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ታምራት ነገራ ደግሞ ብሔራዊነትን ሳይሆን ጎሰኝነትን መሠረት አድርጎ የተመሠረተ የፖለቲካ ሥርዓት ባለበትና የሃይል ሚዛንን ተከትሎ ሚዲያ በሚቆምባት ሐገር የሚዲያ ሚና ዋልታ ረገጥ እንደሆነ አስረድተዋል። 

https://www.youtube.com/watch?v=GE2q3fAyB_A

የጋዜጠኛው ፈተና

በጋዜጠኝነት ሙያ ከ18 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ወይዘሮ አባይነሽ ብሩ በበኩላቸው ወቅቱ የጋዜጠኝነት ሙያ የሚፈተንበት፣ ሙያና ሙያተኛ የሚለዩበት እንደሆነ ጠቅሰው፤ መንግስት ለውጡን ተከትለው የሚመጡ ነፃነቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው በማድረግ ሚዲያው ለለውጡ መሠረት እንዲጥል እድል ማመቻቻት አለበት ብለዋል።

እንዲሁም ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ “ሚዲያዎች ከሚያሰራጩት የመረጃ ብክለት ህብረተሰቡን ለመጠበቅ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እና የተቋማት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ግብረ-መልስ ለመስጠት በአቅምና በፍጥነት ደከም ያሉ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

https://www.youtube.com/watch?v=WL4ZCi4U1z0

የዞን 9 ጦማሪያን የማዕከላዊ ቆይታ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም