ጉባዔው የሚዲያ ማሻሻያ ህግ አለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እንዲወጣ ያግዛል-የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ቡድን

85

ሚያዝያ 22/2011 የዓለም የፕሬስ ቀን ጉባዔ በኢትዮጵያ መካሄዱ አገሪቷ እያከናወነች ያለው የሚዲያ ማሻሻያ ህግ ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እንዲወጣ ያግዛል ሲል የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ቡድን ገለጸ።

የሚዲያ ህግ ማሻሻያ ጥናት ቡድኑ ሊቀ መንበር አቶ ሰለሞን ጎሹ ለኢዜአ እንደገለጹት የዓለም የፕሬስ ቀን ጉባዔ በኢትዮጵያ መከበሩ አገሪቷ እየሰራች ያለው የሚዲያ ማሻሻያ ህግ ዓለም አቀፍ ደረጃው እንዲጠብቅ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

ተቋማቱ ለጉባዔው ወደ ኢትዮጵያ መምጣቻው ደግሞ ተቀራርበውና አብረው በመስራት የህግ ማሻሻያው ዓለም አቀፍ ደረጃውን እንዲጠብቅ ያስችላል ሲሉ ተናግረዋል።

የሚዲያ ህጉ ረቂቅ ጥናቱ አልቆ ለሚመለከታቸው አካላት በ15 ቀናት ውስጥ ይፋ የሚደረግ ሲሆን በጉባዔው የተሳተፉ የአገር ውስጥ ጋዜጠኞችና ተቋማት ከጉባዔው የሚያገኙትን ልምድና ተሞክሮ ይዘው በንቃት እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ እየተወሰደ ያለው ዘርፈ ብዙ የለውጥ እርምጃዎች ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ምቹ የስራ ከባቢ በመፍጠሩ ምክንያት የዘንድሮው የፕሬስ ቀን በአገሪቷ እንዲከበር በማስቻሉ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ቀን ዛሬ ጀምሮ በልዩ ልዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም