የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ የልኳንዳ ቤቶች የዋጋ ጭማሪ የተጋነነ ነው---አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች

87

ሚያዝያ 20/2011 በአዲስ አበባ የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ የልኳንዳ ቤቶች ያደረጉት  የዋጋ ጭማሪ ከፈተኛ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

የኢዜአ  ሪፖርተር ያነጋገራቸው  ሸማቾች እንዳሉት  በዓሉን  ምክንያት  በማድረግ  ልኳንዳ ቤቶች  በፊት ከነበረው ዋጋ በእጥፍ ጨምረውብናል ነው ያሉት፡፡

ከጾሙ በፊት ከ160 እስከ 200 በር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ የከብት ስጋ  በአሁኑ ወቅት እስከ 300 ብር  እየገዙ መሆኑን የተናገሩት በ6 ኪሎ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ወንዶሰን ሀይሉ  ናቸው፡፡

ይሄም ዝቅተኛ ገቢ ላለው የህብረተሰብ ክፍል ከአቅም በላይ እንደሆነ ነው የተናግረው ፤የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ስጋ ቤቶች ተመጣጣኝ ቢሆንም ወረፋ እንዳላቸው ነው የጠቀሱት፡፡

በአሉን ተከትሎ  ልኳንዳ  ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ማድረግ  የተለመደ ቢሆንም የዘንድሮው የተጋነነ መሆኑን የገለጹት ደሞ ወይዘሮ ሸዋዬ  ሀይለመስቀል የተባሉ የከተማው ነዋሪ ናቸው፡፡ 

ከ2 ውር በፊት በ200 ብር ሲሸጥ የበረው አንድ ኪሎ የከብት ስጋ አሁን 350 ብር  በመሸጥ ላይ እንደሆነ በመናገር ነው፡፡

ወይዘሮ ሸዋዬ እንዳሉት  ዶሮ  በ400 ብር እንዲሁም የእንቁላል ዋጋ እስከ 5 ብር    መግዛታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም በምግብ ሸቀጦች  ቅቤ 350 ብር እንዲሁም ቀይ  ሽንኩርት  25ብር በሆነ ዋጋ  መገዛታቸውን ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ እርስ በእርስ በመረዳዳት ፣መጠያየቅና በደስታ እያከበሩ እንደሆነ ነው ያስረዱት፡፡

የአዲስ አበባ የህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው አሊ  እንደገለጹት  ገበያን ለማረጋጋት በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል የምርት ስርጭት በበቂ ሁኔታ መቅረቡንና የግብርና ምርቶችና ሌሎች ግብዓቶች  መቅረባቸውን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም