''የወባ በሽታን ለማጥፋት የተጀመረውን አገራዊ እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት መደረግ አለበት''- የጤና ሚኒስትር ዴኤታ

79

ሚያዝያ17/2011የወባ በሽታን ለማጥፋት የተጀመረውን አገራዊ እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት እንዲደረግ የጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠየቁ።

የወባ በሽታን ለማጥፋት የተጀመረውን አገራዊ እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ የተቀናጀ ጥረት እንዲደረግ የጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ጠየቁ።

በድሬዳዋ ከተማ አገር አቀፍ ዓመታዊ ወባን የመከላከል፣የመቆጣጠርና የማጥፋት ዘመቻ የሥራ እንቅስቃሴ የገመገመው 12ኛው የጤና ጉባዔ  ተጠናቋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታዋ ዶክተር ሊያ ታደሰ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ከአገሪቱ በሽታውን ለማጥፋት በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የጋራ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

ክልሎችና በዘርፉ ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላት የጀመሩትን የተናጠልና የተቀናጀ እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆን መሥራት ይገባቸዋል ብለዋል። 

የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በዘርፉ የሚያደርጉትን  ጥረት ማጠናከር እንዳለባቸው የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ለዚህም ሚኒስቴሩ ድጋፍና ቁጥጥር በማድረግ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አመልክተዋል።

ሚኒስቴሩ ከከፍተኛ ትምህርትና ከምርምር ተቋማት ጋር  ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናከርም አስታውቀዋል።

ባለፉት ስድስት ዓመታት በሽታውን ለመቆጣጠር በህክምና ፣በአጎበር ዕደላ፣ በኬሚካል ርጭትና በግንዛቤ ማስጨበጥ መስኮች የተከናወኑት ተግባራት  ውጤታማ እንደነበሩም ተናግረዋል።

በዚህም በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር በግማሽ መቀነሱን ያስረዱት ዶክተር ሊያ፣በበሽታው የመሞት መጠን ከ80 በመቶ በላይ መቀነሱን ገልጸዋል።

በጉባዔው በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ትኩረት ተሰጥቶት በመገናኛ ብዙኃን ተደግፎ እንዲሰጥ ተጠይቋል። 

በሥራቸው ውጤታማ ለሆኑ አካላት ለሽልማት ተሰጥቷል።

የአፋር ክልል 13ተኛው የጤና ጉባዔ በመጪው ዓመት እንዲያስተናግድ ተወስኗል፡፡ 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም