ቭላድሚር ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሩሲያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጋበዙ

158

አዲስ አበባ ሚያዚያ 19/2011 የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሩሲያን እንዲጎበኙ ጋበዟቸው።

ከሁለተኛው ቤልት ኤንድ ሮድ የመሪዎች ውይይት መድረክ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሁለቱ መሪዎች በሀገራቱ መካከል ስላለው ታሪካዊ ትስስርና በሌሎችም የሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውም ተገልጿል።

በወቅቱም ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዚህ ዓመት በሩሲያ ፌዴሬሽን ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እ.አ.አ በ1943 ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም