ሱዳናውያን የተቃውሞ ሰልፈኞች ከሽግግር ምክር ቤቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አቋረጡ

129
ሚያዚያ 14/2011 ሱዳናውያን የተቃውሞ ሰልፈኞች ኦማር አል በሺርን ከስልጣን አውርዶ ከተቋቋመው ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቋረጣቸውን ተናግረዋል። የሽግግር ምክር ቤቱ የአል በሺር ዘመን “ርዝራዦችን” ያካተተ ስብስብ መሆኑን ሰልፈኞቹ ተችተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን በሀገሪቱ ወታደራዊ ሃይል ዋና መስሪያ ቤት ዙሪያ የተሰበሰቡ ሲሆን የሲቪል የሽግግር ምክር ቤት ስልጣን መረከቡ ይፋ እስከሚሆን በመጠበቅ ላይ ናቸው። የሱዳን ወታደራዊ ሃይል በበኩሉ ስልጣን ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆኑን የገለፀ ሲሆን፤ የወታደራዊና የሲቪል ጥምር የሽግግር ምክር ቤት ሊቋቋም እንደሚችል ተነግሯል። የተቃውሞ ሰልፉን እያስተባበረ የሚገኘው የሱዳን የባለሙያዎች ማህበር የሲቪል የሽግግር ምክር ቤት እንዲቋቋም አበክሮ መጠየቁ ይታወሳል። የባለሙያዎቹ ማህበር ባሳለፍነው ቅዳሜ ከወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ጋር መወያየቱ ተጠቁሟል። ምንጭ፦ቢቢሲ  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም