በዩክሬን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ኮሜዲያኑ ዘለንስኪ አሸነፉ

171

ሚያዚያ 14/2011 ዩክሬናዊው ኮሜዲያን ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው በሰፊ ልዩነት አሸንፈዋል።

ለሀገሪቱ ፖለቲካ አዲስ የሆኑት የኮሜዲ ተጫዋቹ ዘለንስኪ በምርጫው ከ70 በመቶ በላይ ድምፅ ማግኘታቸው ነው የተነገረው።

የ41 ዓመቱ ዘለንስኪ ከወቅቱ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ፔትሮ ፖሮሼንኮ ጋር ተፎካክረዋል።

ፖሮሼንኮ በምርጫው መሸነፋቸውን ያመኑ ሲሆን፤ "አዲሱ ልምድ የሌላቸው የዩክሬን ፕሬዚዳንት በሩሲያ ጫና ውስጥ ይወድቃሉ" ሲሉ ተናግረዋል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ አዲሱ የዩክሬን አመራር በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጉዳዮች ላይ የመራጮቹን ተስፋ እውን ለማድረግ መስራት እንዳለበት ገልጿል።

አዲሱ የምርጫ አሸናፊ ዘለንስኪ ደግሞ በቀጣይ ከተገንጣይ ወገኖች ጋር ውይይት እናደርጋለን ብለዋል።

የዩክሬን ግዛት የነበረችው ክሬሚያ በፈረንጆቹ 2014 ወደ ሩሲያ መገንጠሏ ይታወሳል።

ከክሬሚያ መገንጠል በኋላ የዩክሬን ወታደራዊ ሃይሎች እና በሩሲያ የሚደገፉ ተገንጣይ ሃይሎች ውጊያ ላይ ናቸው።

ምንጭ፦ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም