የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በደምቢዶሎ ከተማ ከህብረተሰቡ ጋር እየተወያዩ ነው

74

አዲስአበባ ሚያዚያ 11/2011 የጨፌ ኦሮሚያ ትናንት የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ የሾማቸው አቶ ሽመልስ አብዲሳ በደምቢዶሎ ከተማ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው።

ትናንት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት አቶ ሽመልስ ዛሬ በቄለም ወለጋ ዞን በደምቢዶሎ ከተማ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እያደረጉ መሆኑን ኦቢኤን ዘግቧል።

የጨፌ ኦሮሚያ ትናንት ባካሄደው አምስተኛ የስራ ዘመን አራተኛ ዓመት አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ሽመልስን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ  በሙሉ ድምፅ መሾሙ ይታወሳል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ ከህብረተሰቡ ጋር የሚያደርጉት ውይይት የሚያተኩረው በወቅታዊ፣ ኢኮኖሚ፣ በሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ መሆኑ ተጠቁሟል።

አቶ ሽመልስ ለክልል ምክትል ፕሬዝዳንትነት እስከ ተመረጡበት ጊዜ ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አቶ ሽመልስ ትናንት መከላከያ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙትን አቶ ለማ  መገርሳን መተካታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም