በሃዋሳ ተቃጥለው የነበሩ ሱቆች በአዲስ መልክ ተገንብተው ነጋዴዎች እንዲረከቡ ተደረገ

70

ሃዋሳ - ሚያዚያ 10/2011 የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከስድስት ወራት በፊት ተቃጥለው የነበሩ ሱቆች በአዲስ መልክ አስገንብቶ ለነጋዴዎች አስረከበ፡፡

በተለምዶ አሮጌ ገበያ በመባል የሚታወቀውና የከተማው ትልቁ ገበያ  መስከረም 29/2011 ዓ.ም.ነበር ደንገተኛ ቃጠሎ የደረሰበት፡፡

የከተማው አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ተስፋዬ ርክክቡ  ማምሻውን በተካሄደበት ወቅት እንደገለጹት 730 ሱቆችን በውስጡ ያካተተው የገበያው ስፍራ  ግንባታ  40 ሚሊየን ብር የፈጀ ነው።

ለግንባታው የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞችና አመራሮች፣ የንግዱ ማህበረሰብና የእምነት ተቋማት ድጋፍ ማድረጋቸውም ተመልክቷል።

በርክክብ ስነስርዓቱ የከተማው ምክትል ከንቲባ ፣  የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም