የምርት ጥራት በማስጠበቅ ለገበያ ማቅረብ የሚያስችል አሰራር እየተተገበረ ነው

140

ሚያዝያ 10/2011 የሀገር ውስጥ ምርቶችን ጥራት በማስጠበቅ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡

ከዓለም ባንክ በተገኘ 50 ሚሊዮን ዶላር ብድር የሀገር ዉስጥ ምርቶችን ጥራት በማስጠበቅ ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል የአሰራር ስርአት ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

አዲሱ የጥራት ማስጠበቂያ መሰረተ ልማት በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ጥራታቸው  ተጠብቆ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የሚያስችል መሆኑም ታውቋል።

ፕሮጀክቱ በተለይ በጨርቃጨርቅ፣ አልባሳት እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በጥራት ተመርተው ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የማይተካ ሚና እንዳለውም ተገልጿል።

በንግድ ሚኒስቴር የፕሮጀክት መሰረት ልማት ስራ ሃላፊ አቶ አባተ አራጋዉ ለኢዜአ እንደገለጹት ከዚህ በፊት በዘርፉ የምርት ጥራት ችግር በስፋት ይስተዋል ነበር።

ይህ መሆኑ ደግሞ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች በዋጋቸው ተወዳዳሪ እንደሆኑ እንከን በመፍጠር በውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይም አሉታዊ ተፅእኖ እንደነበረው አስታውሰዋል።

አሁን ግን የምርት ጥራት ማስጠበቂታ ፕሮጀክት መርሃ ግብር ተግባራዊ መደረጉ ቀደም ሲል ይስተዋል የነበረውን ችግር በዘላቂነት ይፈታዋል ነው ያሉት።

የፕሮጀክቱ የሙከራ ትግበራ የተጀመረው ባለፈው ዓመት መሆኑን የጠቆሙት ሃላፊው አሁን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ተደርጓል ብለዋል።

የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው የምርት ጥራት ማስጠበቂያ መሰረተ ልማት ማለት ከአገር ውስጥ የግብይት የትብብር ሂደት እስከ ዓለም አቀፍ የገበያ ሰንሰለት በጥራት የማቅረብ ሂደት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም