ያለፈው መጋቢት ወር ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የሙቀት መጠን በሁለተኝነት ተመዝግቧል

73

ሚያዝያ 09/ 2011 ያለፈው መጋቢት ወር ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የሙቀት መጠን በሁለተኛነት እንደተመዘገበ ኮፐርኒከስ የተሰኘው የአውሮፓ አርዝ ኦብዘርቬሽን ፐሮግራም ያወጣውን ወርአዊ ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል።

መጋቢት ወር ከእስካሁኑ በተለየ መልኩ በሁለተኛ ደረጃ ሙቀት የተመዘገበበት ወቅት ስለመሆኑም ዘገባው ጠቅሷል፡፡

በዘገባውም በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ክፍሎች ያለው እርጥበታማ እና ከባድ ዝናብ  ሁኔታ  ሲታይ በአማካይ በቀጠናው ድንገተኛ የሆነ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሊያስከትል ይችላል፡፡

ባሳለፍናቸው ሶስት ተከታታይ  ሳምንታት በአብዛኛዎቹ የኢራን የሃገሪቱ ክፍሎች ዝናባማ ሁነው እንደቆዩ ዘገባው ያሳያል፡፡

የሰሜን-ምስራቅ ጎልስታን ግዛት አካባቢ ሃገሪቱ በአንድ ዓመት ከምታገኘው አማካይ ዓመታዊው የዝናብ መጠን ውስጥ በቀን 70 በመቶውን የሚሸፍን ከፍተኛ የሆነ የዝናብ ታገኛለች ይላል ዘገባው፡፡

በአሁኑ ወቅትም ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የግድቦቹ 95% በመቶ መሙላት መቻላቸው ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሊከሰት ይችላል ሲል ዘገባው ስጋቱን ያስቀምጣል፡፡

ስለሆነም ኢዳ የሚል መጠሪያ የተሰጠው አውሎ ንፍስ በምስራቅ አፍሪካ ጭምር አውዳሚ የሆነ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና ከፍተኛ መጠን ያለው የህይወት ጥፍት አስከትሏል በማለት ዘገባው ይጠቅሳል፡፡

በዚህ አውሎ ንፍስም ቢያንስ ከ850 በላይ የሚሆኑ ንፁሃን ዜጎች ሰዎች ህወታቸውን እንዳጡ ተገምቷል፡፡

እንደ ሞዛምቢክ፣ ማላዊ እና ዚምባብዌ ያሉ ሃገሮች ልክ ማዳጋስካርን አጋጥሟት እንደነበረው አይነት ያለ  አውሎ ንፋስ ክፉኛ ተጎድተዋል በማለት ዘገባው ያትታል፡፡

ስለሆነም ይላል ዘገባው በዓለም ላይ ስላለው የግግር በረዶ ሁኔታ የዘርፍ ባለሙያዎች ምልከታቸውን ሲያስቀምጡ ከ1960 ጀምሮ የበረዶ ግግር ውፍረት ከ22 ሜትር በላይ ጉዳት እየደረሰበት ያስረደሳሉ በማለት ያስቀምጣል፡፡

ባለፈው ሳምንት የዘርፍ የሳይንስ ሊህቃንን ምልከታ ዋቢ በማድረግ ዘገባው ሁኔታውን ለመዳሰስ እንደሞከረው  ባሳለፍናቸው  አስርት ዓመታት የበረዶ ንጣፍ መሳሳቱን ተከትሎ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ እስከ 30 በመቶ የሚሸፍን የባህር ከፍታ እንዲጨምር አድርጎታል በማለት ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም