የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 800 ኮምፒዩተሮች ለትምህርት ቤቶች ደጋፍ አደረገ

90

ሚያዝያ 9/2011 የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ካማራ ኤጁኬሽን ኢትዮጵያ ከሚባል ግብረሰናይ ድርጅት ያገኘውን 800 ኮምፒዩተሮችን በባሌና ምዕራብ አርሲ ዞኖች ለሚገኙ 40 ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ ተማሪዎች ከቴክኖሎጂ ጋር እንዲተዋወቁ በማድረግ የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ  እገዛ እንደሚያደርግ ድጋፉን ያገኙ ትምህርት ቤቶች ገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ  ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አቡበከር ከድር  በርክክቡ ስነስርዓ ወቅት እንደገለጹት በድርጅቱ  ያገኟቸውን    

ኮምፒተሮች  ቡለቱ ዞኖች  ጥረት ላለባቸው 40 ትምህርት ቤቶች  አገልግሎት እንዲውሉ  ተከፋፍሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ ከሌሎች ተባባሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በጥናት ለይቶ ለመደገፍ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለትምህርት ቤቶቹ የተደረገው ድጋፉም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን የገለጹት ዶክተር  አቡበከር   የተገኘው የኮምፒዩተር ድጋፍ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት እንዳለው አመልክተዋል።

የባሌ ዞን ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ግዛው በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲና ድርጅቱን ለዳረጉት ድጋፍ አመስግነው ይህም   በተለይ  የመማር

ማስተማሩን  ስራ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

 በዩኒቨርሲቲው በኩል ለትምህርት ቤቶቹ የተከፋፈሉት  ኮምፒውተሮች ለመማር ማስተማሩ ሂደት አጋዥ የሆኑ እንደ ማጣቀሻ  መፅሃፍት  የሚያገለግሉ

መረጃዎች  የተጫነላቸው መሆኑን ያስታወቁት ደግሞ  የካማራ ድርጅት ተወካይ አቶ ሚኪያስ ተስፋዬ ናቸው፡፡ 

ድርጅታቸው በሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት ከ2ሺህ ለሚበልጡ ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ ድጋፍ መድረጉን  አስታውሰው ወደፊትም 

ከመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጀመሩትን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

ከምዕራብ አርሲ ዞን ድጋፉን ካገኙት ትምህርት ቤቶች መካከል የቆሬ መሰናዶ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር  አቶ ጀማል ከድሮ  " የተሰጠን ድጋፍ 

ተማሪዎቻችን ከቴክኖሎጂ ጋር በቅርበት እንዲተዋወቁና የትምህርት ጥራትም ለማረጋገጥ እገዛ ያደርገሉ" ብሏል፡፡

''በድጋፍ የተገኙት ኮምፒዩተሮች የማጠቀሻ መጽሐፍት  ለትምህርት አጋዥ የሆኑ ሶፍት ኮፒዎች የተጫኑላቸው መሆናቸው  ትምህርት ቤቱ

ለመጻሀፍት ግዥ ያወጣ የነበረውን ወጪ  ያስቀራል "  ያሉት ደግሞ ከባሌ ዞን ጎባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ ገንዘቤ ከድር ናቸው፡፡

የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ ስራ በተጓዳኝ 100  የሚሆኑ ምርምሮችና ማህበረሰብ አቀፍ ፕሮጄክቶችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ  ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም