የአዲስ አበባ አስተዳደር ነዋሪዎች ለተፈቃዮች ማቋቋሚያ ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

62

ሚያዝያ 7/2011 በአዲስ አበባ የሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጆችና ባለሀብቶች ለክልሉ ተፈናቃዮች መርጃ ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ ወገኖች ማቋቋሚያ 10 ሚሊዮን ብር ለግሷል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ ትናንት በጎንደር ከተማ ድጋፉን አስረክበዋል፡

ድጋፉን ያደረጉት የቂርቆስና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ነጋዴዎች ናቸው፡፡

ክፍለ ከተሞቹ  6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ቆርቆሮ፣ ሚስማር እንዲሁም የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አበርክተዋል፡፡

አስተዳደሩ በበኩሉ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም 10 ሚሊዮን ብር መስጠቱንም  ኢንጂነር እንዳወቅ ተናግረዋል፡፡

አንድ ባለሀብት 10 ተፈናቃይ ህጻናት ዩኒቨርሲቲ ገብተው ትምህርታቸውን እስኪያጠናቅቁ ድረስ በየወሩ10 ሺህ ብር ለመገለስ ቃል መግባታቸውንም ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፤ ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽነር አቶ አማረ ክንዴ የክልሉ መንግሥት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ በዘላቂነት የሚያቋቁም  መርሐ ግብር መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

በክልሉ ከ90ሺህ በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም