የደም የማሰባሰብ ስራ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

63

ሚያዝያ 7/2011 አማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደርና ሰሜን ሸዋ ዞኖች  በተከሰተው የጸጥታ ችግር ለተጎዱ ሰዎች በኮምቦልቻ ከተማ ደም እየተሰባሰበ ነው፡፡

በዞኖቹ  በተፈጠረው ችግር በራሳቸው ተነሳሽነት ደም እያሰባሰቡ ያሉት ወጣቶች መሆናቸውን የደሴ ደም ባንክ አገልግሎት ባለሙያ አቶ ኪዳነማሪያም ወርቁ ለኢዜአ አስታውቀዋል፡፡

ለአንድ ሳምንት በሚቆየው ልገሳ መርሐ ግብር ከበጎ ፈቃደኞች እስካሁን 5 ሺህ ዩኒት ደም ለተጠቃሚዎች ተሰጥቷል፡፡

በቆይታውም  10 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱን አስረድተዋል።

ወጣቶቹ ኅብረተሰቡን በማስተባበር በደም እጦት የሚሞቱ ሰዎችን ለመታደግ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ባለሙያው  ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ደም ለጋሾች ማህበር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ ይርጋ ማህበሩ ወጣቶችን በማስተባበር የደም ልገሳውን በማስተባበርና በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

በግላርቸው ለ84 ጊዜ ደም መለገሳቸውን የተናገሩት አቶ ሙሉጌታ፣ በዚህም ውስጣዊ እርካታ ይሰማኛል ብለዋል፡፡

በከተማው የ01 ቀበሌ ነዋሪ ወጣት ሙሐመድ ዓሊ በበኩሉ በደም እጦት የሚሞቱ እናቶችና ህጻናትን ለመታደግ የማህበሩ አባል በመሆን ለሦስተኛ ጊዜ ደም መለገሱን ተናግሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ ደም ልገሳ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ተማሪዎችና ማህበረሰቡ እየተሳተፉ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም