የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ተመረጠ

57

አዲስ አበባ ሚያዝያ 5/2011 በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ ተመረጠ።

አቶ ሙሳ አደምን ሰብሳቢው ሆነው ሲመረጡ አቶ ግርማ በቀለ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል።

ዶክተር ፋሪስ ኢሳያስ የጋራ ምክር ቤቱ ጸሐፊ ሆነው ተመርጠዋል።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ዛሬ በመሩት መድረክ በተካሄደ ምርጫ፤ በጠቅላላው 107 ፓርቲዎችን ያሰባሰበው የጋራ ምክር ቤቱ የአፋር ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ሙሳ አደም ሰብሳቢ ሆነዋል።

አቶ ቀጀላ መርዳሳ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) እና አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከአቶ ሙሳ አደም ሙሳ ጋር በእጩነት ቀርበው ነበር።

አቶ ሙሳ 44 ድምፅ በማግኘት ነው የተመረጡት።

የጋራ ምክር ቤቱ ፓርቲዎቹን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚመራ የቃል ኪዳን ሰነድ የትግበራ ሂደትን ይከታተላል፤ በፓርቲዎች መካከል የሚፈጠር አለመግባባትን የመፍታት ጥረትም ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም