በመላው የኦሮሚያ የስፖርት ጨዋታዎች ምዕራብ ሸዋን የሚውክሉ ተወዳዳሪዎች ተመረጡ

198

አምቦ ሚያዝያ 3/2011 በቅርቡ ነቀምቴ ከተማ በሚካሄደው የመላው ኦሮሚያ የስፖርት ጨዋታዎች ላይ በምዕራብ ሸዋ ዞንን ወክለው የሚሳተፉ 86 ምርጥ ተወዳዳሪዎች ተመረጡ፡፡

የተወዳዳሪዎቹ የተመረጡት በአምቦ ከተማ ሲካሄድ በሰነበተው ዓመታዊ የወረዳዎች የልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ላይ ነው፡፡

በቦሊቦል፣ በእግር ኳስ ፣  እጅ ኳስ፣  ቴኒስ፣  ቼዝ ፣ ዳርትና አትሌቲክስ  በሁለቱም ጾታ ከአንድ ሺ በላይ  ስፖርተኞች ሲሳተፉበት የቆየው ውድድሩ  ዛሬ ተጠናቋል።

ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ሆማቾ አሙኔሼን ኢንጂነሪንግ እና ግሎባል ኮሌጅንና የአምቦ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ 22 ወረዳዎች ተሳትፈዋል፡፡

በማጠናቀቂያው ላይ በተካሄዱ ውድድሮች በወንዶችና በሴቶች ቴኒስ ፣ እጅ ኳስና በዳርት ጨዋታዎች  የኤጄሬ ወረዳ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል ።