በትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

139

ሚዛን  ሚያዝያ 3/2011 በካፋ ዞን በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።

በካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ መረጃ ትንተና ባለሙያ ሳጅን ግርማ መቻሎ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው ዛሬ ጠዋት 2:00 ላይ የደረሰው በካፋ ዞን ጊንቦ ወረዳ ነው።

የመገልበጥ አደጋ የደረሰው ከቦንጋ ወደሚዛን ሲጓዝ በነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ 3-12227 ደህ የሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ላይ ነው።

" በአደጋውም የአምስት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በሌሎች 15 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል" ብለዋል።

ሳጅን ግርማ እንዳሉት አደጋው የደረሰበት ቦታ ጠመዝማዛ መሆን፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከርና ከመኪናው አቅም በላይ መጫን ለአደጋው መከሰት ምክንያት ሆኗል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቦንጋ ገብረጻዲቅ ሻዎ ሆስፒል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም