በኮምቦልቻ አውቶብስ መናኸሪያ 880 ጥይት መያዙን ፖሊስ ገለጸ

124

ደሴ ሚያዚያ 2/2011 በኮምቦልቻ አውቶብስ መናኸሪያ 880 የክላሽንኮቭ ጠመንጃ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ኮማንደር ያለለት ዘገየ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት ህገ-ወጥ ጥይቱ በቁጥጥር ስር የዋለው ዛሬ ረፋዱ ላይ ነው።

ከባቲ መጥቶ ወደ ሸዋ ሮቢት ሊሸጋገር ሲል ከምቦልቻ መናኸሪያ ውስጥ በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን ተናግረዋል።

ከጥይቱ በተጨማሪም 400 ሺህ ብር የያዘ የባንክ አካውንት አበሮ መያዙን ጠቁመው፤ ህገ-ወጥ ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባለው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችንና ጥርጣሬ የሚያሳድሩ ጉዳዮችን ሲመለከት ለፀጥታ መዋቅሩ የመጠቆም ለምዱን አጠናክሮ እንቂቀጥልም ኮማንደር ያለለት አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም