የእናቶች ቀን በዓል በመቀሌ ተከበረ

170

መቀሌ መጋቢት 29/2011 ''ክብርና ምስጋና ለእናት!''በሚል መሪ ቃል ዛሬ የእናቶች ቀን በዓል በመቀሌ ተከበረ።

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተኽላይ ወልደማርያም እንዳሉት በእናቶች ላይ የሚደርሰውን ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግር መፍታት የዜጎች ኃላፊነት ነው።

የእናት ውለታ በቃላት ማሞካሸት ብቻ ሳይሆን፤ በልማቱና ሰላም ያበረከቱት አስተዋፅኦ በማጉላትም ተገቢውን ክብርና ምስጋና ማግኘት ይገባቸዋል ብለዋል።

ቢሮው እናቶች ጤንነታቸው ተጠብቆና ጤንነቱ የተጠበቀ ብቁ ዜጋ በማፍራት እያደረጉት ያለው ሚና መከበርና መወደስ እንዳለበትም ገልጸዋል።

የእናቶች ለእናቶች ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ አስመላሽ እንዳሉት ድርጅቱ እናቶች የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለማቃለል ሥልጠና በመስጠት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በዓሉ ለ18ኛ ጊዜ በባህላዊ ጨዋታዎች፣ በስፖርት ትርዒቶችና በመሰል ዝግጅቶች በሰማዕታት ሐውልት ተከብሯል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም