እንግሊዝ ከህብረቱ የመውጫ ጊዜ ወደ ሰኔ 30 እንዲራዘምላት የአውሮፓ ህብረትን ጠየቀች

52

መጋቢት 27/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ቴራዛ ሜይ የአውሮፓ ህብረት የእንግሊዝን ከህብረቱ የመውጫ ጊዜ ወደ የፊታችን  ሰኔ 30 እንዲያራዝምላቸው በደብዳቤ ጠየቁ፡፡

ከዚህ በፊት እንግሊዝ ከህብረቱ በምትወጣበት ጉዳይ ላይ ለመወሰን እአአ ለሚያዚያ  12 / 2019 ቀጠሮ ተይዞ የነበር ቢሆንም በፓርላማ አባላቱ መካከል ስምምነት ላይ አለመደረሱ ሜይ የይራዘምልን ደብዳቤ ለመፃፍ ምክንያት እንደሆናቸው ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሯ የፓርላማ አባላቱ በቅርብ ጊዜ  ስምምነት ላይ ከደረሱ የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ ምርጫ ከሚያደርግበት እአአ ግንቦት 23 /2019 በፊት አገራቸው ከህብረቱ መነጠል እንደምትችል ተናግረዋል፡፡

ስምምነት ላይ ለመድረሳቸው እርግጠኛ መሆን ስላልቻሉ ለአውሮፓ ህብረት የፓርላማ ምርጫ እንግሊዝ እጩዎችን ለማቅረብ ዝግጁ መሆኗንም አክለው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም