የቀድሞው የጋምቢያ ፕሬዚዳት ያያህ ጃሜህ በ22 ዓመት የስልጣን ቆይታቸው 362 ሚሊዮን ዶላር መዝብረዋል

50

መጋቢት 27/2011 የጋምቢያ መንግስት ባወጣው ሪፖርት ያያህ ጃሜህ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1994 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠሩበት ግዜ ጀምሮ በ2017 ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከመሸሻቸው በፊት ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት 632 ሚሊዮን ዶላር መዝረፋቸውን ይፋ አድርገዋል፡

የሀገሪቱ መንግስት ለሁለት ዓመታት በቀድሞ ፕሬዚዳንቱ ሲያደርገው የነበረውን ምርመራ ተከትሎ የፍትህ ሚኒስትሩ አቡባካር ታምባዱ እንዳስታወቁት ወንጀሉን ለማጣራት ከ253 የአይን ምስክሮች ቃለ መጠየቅ ተደርገዋል፡፡

በምርመራው ሂደት ያያህ ጃሜህ 362 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መዝረፋቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ይህን ያህል ገንዘብ መመዝበሩ በአገሪቱ ዜጎች ህይወት የሚያሳድረው ተፅእኖ ቀላል አይደለም ብለዋል ፍትህ ሚኒስትሩ ፡፡

ያያህ ጃሜህ ካሉበት ኢኳቶሪያል ጊኒ በሪፖርቱ ዙሪያ ያሉት ነገር ባይኖርም የእሳቸው ደጋፊዎች አሁንም ሪፖርቱ እውነታ የለውም በማለት እያያጣጣሉት ነው፡፡

አዲሱ የጋምቢያ ፕሬዚዳንት ባሮው አስተዳደር ያያህ ጃሜህ ውድ መኪኖችን ጨምሮ የተለያዩ ሃብቶችን ይዘው ሸሽተዋል ብሎ የሚያምን ሲሆን፤ የተዘረፈውን ገንዘብ ለማስመለስ እሰራለሁ ብለዋል፡፡

ያያህ ጃሜህ ገንዘቡን የዘረፉት በማእከላዊ ባንክ የሃሰተኛ የሂሳብ ደብተር በመክፈት እና ቴሌኮሙኒኬሽን ከመሳሰሉ የፌደራል ተቋማት በማጭበርበር መሆኑም ተገልጸዋል፡፡

ያያህ ጃሜህ እአአ በ2016  በሀገሪቱ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቻን ተከትሎ ስልጣናቸውን  ለማስረክብ  አንገራግረው  የነበረ ቢሆንም የአፍሪካ ህብረትና በምዕራብ  አፍሪካ የኢኮኖሚ  ማህበረሰብ  ወታደራዊ  እርምጃ  እንደሚወስዱ በማሳወቃቸው  እአአ በ2017 ወደ ኢኳተሪያል ጊኒ ለመሸሽ ተገደዋል፡፡

ምንጭ፡- አፍሪካ ኒውስ ነው

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም