ፓርቲው አመራሩን መረጠ

242

ጅግጅጋ  መጋቢት 25/2011 የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ሶዴፓ) አቶ አህመድ ሺዴን ሊቀመንበሩ አድርጎ መረጠ።

አቶ አህመድ ፓርቲውን እንዲመሩ የተመረጡት ከ61 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መካከል ነው።

አቶ አህመድ ዛሬ ስያሜውን የቀየረውን የሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ሶሕዴፓ)በሊቀመንበርነት ሲመሩ ቆይተዋል።

ተመራጩ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ(ኢፌዴሪ)የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው።

የክልሉን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ፓርቲው ሊቃመናብርቱን ጨምሮ ዘጠኝ አባላትን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውንም ሰይሟል።

ፓርቲው ባወጣው አዲስ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5 መሠረት የማንኛውም ብሄር ተወላጅ የፓርቲው አባል መሆን ይችላል።

የኦዲትና ክትትል ኮሚቴ አባላት ምርጫ ውጤት እየተጠበቀ ነው።

ሶዴፓ ከመጋቢት 23 ቀን 2011 ጀምሮ ድርጅታዊ ጉባዔውን በጅግጅጋ ከተማ እያካሄደ ነው።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ በፓርቲው ጉባዔ ማጠቃለያ ላይ ንግግር ለማድረግ ጅግጅጋ ገብተዋል።