የጤና ሚኒስቴር የጤና ፖሊሲውን ለማሻሻል የመጀመሪያውን ንድፈ ሀሳብ ለባለድርሻ አካላት አቀረበ

114

አዲስ አበባ  መጋቢት 24/2011 የጤና ሚኒስቴር የጤና ፖሊሲውን ለማሻሻል የመጀመሪያውን ንድፈ ሀሳብ ለባለድርሻ አካላት አቀረበ።

ሚኒስቴሩ  የአንድ ዓመት የስራ ዕቅድ አፈጻጸሙን ሪፖርት የጤና ተቋማቱ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት አቅርቧል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ዶክትር ሊያ ታደሰ  በዓመቱ የተሰሩ ጠንካራና ደካማ ስራዎች እንዳሉ ገልጸዋል።

እስካሁን ከተከናወኑት ተግባራትም በተለይም  የሴት አመራሮች በተለያዩ የጤና ተቋማት ገብተው ግማሽ በመቶውን የዘረፉ የስራ ድርሻ ወስድው በመስራት ውጤታማ ስራ መስራታቸው በበጎ ጎኑ አስታውሰዋል።

እንደ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገለጻም የሰው ሃይል እጥረት፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት በመደሃኒት  አቅርቦት ላይ ያደረሰው ጫና፤ የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች ዝውውር፣ የአመራር በየጊዜው መቀያየርና የጸጥታ ችግሮች በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች መከሰቱ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለው ጫና በዓመቱ በተዳግዳሮት የተነሱ ናቸው።

በተለይም  በተለያዩ አካባቢዎች በፀጥታ ችግር የተፈናቀሉ ማህበረሰቦች ለደረሰባቸው የጤና ችግር ባለሙያዎችን ማሰማረታችን በመደበኛ ስራችን ላይ ጫና አድርሷል ብለዋል።

እነዚህን ችግሮችን በቀጣይ ለመፍታትም ሁሉም በየዘረፉ ያሉ አካላቶች ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው  አሳስበዋል።

በባለሙያዎች በደመወዝና ጥቅማጥቅም ዙሪያ የሚያነሱ ጥያቄዎችም እንደሚሰሩበት ነባራዊ ሁኔታ ጉዳዩ ታይቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገቢውን ምላሽ እንደሚያኝም ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም አዲስ እየተዘጋጀ ያለውን የጤና ፖሊሲ ለማሻሻል ንድፈ ሃሳቦችን፤ ረቂቂ ጉዳዮችንና ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማሰባሰብ ለባለድርሻ አካላት አቅረበዋል።

ከባለድርሻ አካላት ውይይትም ግብዓት ሰብስበው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደስራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

አዲስ የሚዘጋጀው የጤና ፖሊሲ በተለይም በከፍተኛ ደረጃ የሚስተዋለውን የህፃናት መቀንጨርን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

ነባሩ የጤና ፖሊሲ ለበርካታ አመታት ሲያገለግል በመቆየቱ አሁን ያለውን  ነባራዊ  ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ  ያላስገባ  መሆኑም በጥናት በመረጋገጡና መሻሻል ያለበቸው ጉዳዮች በመገኘታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት  አምነውበት ተሻሽሎ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባም ተገልዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም