1ኛ ዓመት የኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከበረ

101

አዲስ አበባ   መጋቢት  24/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ኃላፊነት የመጡበት 1ኛ ዓመት በሚሊኒየም አዳራሽ ''ከመጋቢት እስከ መጋቢት የለውጥ መዘከሪያ'' በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በዛሬዋ እለት ነበር በህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት በመቅረብ ቃል ገብተው ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ  ስልጣኑን የተረከቡት።

365 ቀናትንና የለውጥ ጉዞን  አስመልክቶ በሚካሄደው በዚሁ ስነ-ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ  ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች በመድረኩ የቀረቡ ሲሆን በአንድ ዓመቱ የቆይታ ጊዜ ውስጥ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችም ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም