የተካሄደው ትግል ከምር እንጂ ለጊዜያዊ ማጭበርበር አይደለም-ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ

89

አዲስ አበባ መጋቢት 22/2011 "የክልሉን ህዝብም ሆነ መላው የኢትየጵያን ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል ከሚሰራው ስራ ውጭ ስለ ዴሞግራፊ መለወጥ የሚወራው የተሳሳተ አረዳድ መሆኑን  የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት ለማ ከባልደረቦቹ ጋር ነፍስ አስይዘው ለአገሪቷና ለህዝቡ ከመታገል ውጭ የማታለል ስራ እንደማይሰሩም አረጋግጠዋል።ፕሬዚዳንቱ በክልሉ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ፕሬዝዳን ለማ ከባለሀብቶቹ ጋር ባደረጉት ውይይት ካነሷቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ስለ ከተማ ስርጭት (ዴሞግራፊ)፣ ስለ ተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ ስለ ኢትዮጵያዊነት፣ ስለ ኦሮሚያና አማራ ህዝቦች(ኦሮማራ)፣ ስለ ኦዲፒና አዴፓ ግንኙነት፣ ስለ ኦዲፒ የአመራር አንድነት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች አንስተዋል።

https://youtu.be/aRcwz7z_Ag4

በተለይም በውይይቱ ወቅት ከተሳታፊዎች "ፕሬዚዳንቱ ዴሞግራፊን ለመለወጥ ሰርታችሁኋል" ተብለው ስለተወራባቸው ጉዳይ ሲመልሱ  ከነባልደረቦቻቸው ለኢትዮጵያ አንድነት የሰሩትና የለፉት ዝናና ዕውቅና ፍለጋ ወይም ለማጭበርበር እንዳልሆነና አገሪቷ ከገባችበት ችግር እንዲትወጣ ነፍሳቸውን ጭምር አስይዘው ሲታገሉ እንደነበር ነው ያወሱት።በወቅቱም ክልሉ በሰፊው ስለሚናጥበት የጸጥታ ችግር መሆኑንና ስለኢኮኖሚ አለመሆኑን በማውሳት፤ ስለኢትዮጵያዊነት ሲናገሩም ለሽወዳ አለመሆኑን በማስረገጥ።

https://youtu.be/YMuqAACvzoI

ከወራት በፊት የተናገርኩት ቢሆንም ከአውዱ ውጭ በራሳቸው መንገድ ትርጉም ሰጥተው የፈጠሩት የተሳሳተ አረዳድ እንጂ የእኔ አስተሳሰብና አመለካከት አይደለም ብለዋል ፕሬዘዳንት ለማ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም