በኦሮሚያ ክልል ኢንቨሰትመንትን ለማነቃቃት ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

60

አዲስ አበባ መጋቢት 21/2011 በኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንትን ለማነቃቃት ያለመ  ኮንፈረንስ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

'የኦሮሚያ ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ የሰላም ኮንፈረንስ' በሚል መሪ ሃሳብ አዲስ አበባ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይ የክልልና የወረዳ አመራሮች እንደዚሁም በርካታ ባለኃብቶች ተሳትፈውበታል።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) የገጠር ዘርፍ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ጽሁፍ እያቀረቡ ሲሆን የኮንፈረንሱ ትኩረት የክልሉን ኢንቨስትመንት ማነቃቃት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም