ማንኛውም ዜጋ በእኩልነት የሚኖርባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ኦዴፓ ይሰራል-ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ

59

አዲስ አበባ መጋቢት 17/2011 ማንኛውም ዜጋ በእኩልነት የሚኖርባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ይሰራል ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።

ፓርቲው የተመሰረተበት 29ኛ ዓመት በዓል የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተከብሯል።

በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር፤ ዜጎች 'የኔ ነው' ከሚል መገፋፋት ወጥተው 'የእኛ' ወደሚል አብሮነት እንዲሸጋገር ጥሪ አቅርበዋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሊቀመንበር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለውጥ ሁሉ ፈተና እንዳለው ገልጸው ፈተናውን በጋራ በመሰለፍ መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ያልተመለሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ለመስራት ሁሉም መነሳት እንደሚጠበቅበትም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም