የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ህግ እየረቀቀ መሆኑን ተገለጸ

165

አዲስ አበባ መጋቢት 14/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ህግ እያረቀቀች መሆኑን ተናገሩ።

በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት "አዲስ ወግ" በሚል ርዕስ የተካሄደው አገራዊ መድረክ በሁለተኛ ቀን የከሰዓት በኋላ ውሎ "የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ፣ ማጽናት፣ ተግዳሮቶችና የቀጣይ አቅጣጫዎች" በሚል ርዕስ ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድንገት ተገኝተዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ አጋጣሚ ባስተላለፉት መልዕክት በፌስ ቡክ የሚሰራጩ ሃሰተኛ መልእክቶች በአገሪቱ ሰላም ላይ እክል እየፈጠሩ በመሆኑ ህጉን ማርቀቅ አስፈልጓል።

በዚህም ከፌስቡክና ከሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ ተወካዮች ጋር ንግግር መጀመሩን ገልጸዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሃገሪቱን ሰላም የሚያውኩ ሃሰተኛ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ ሊቆጠቡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ማህበራዊ ሚዲያው በጠቅላላ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ከሆነ ውይይት ተደርጎበት የማያዳግም መፍትሄ እንደሚበጅለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም