የፌዴራል ዳኞች አስተዳዳር ጉባኤ ላይ ማሻሻያ ሊደረግ ነው

68

አዲስ አባባ መጋቢት 14/2011 የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ እንደገና ሊሻሻል ነው።

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደርን በአዲስ መልክ ለማደራጀት የሚያስችል የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ተጠናቆ ከባለሙያዎች ጋር ውይይት እየተደረገበት ነው።

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ እንዳሉት፤ ነባሩ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አዋጅ ውስንነት እንደነበረበት ገልጸዋል።

በዚህም ሳቢያ ነባሩ አዋጅ ሙሉ በሙሉ እንዲሻሻል ተደርጓል ብለዋል።

አዲስ የተረቀቀው አዋጅ የፍርድ ቤቶች ዳኞች ስራቸውን ከውስጣዊና ከውጫዊ ተፅዕኖ ነጻ ሆነው እንዲደርሱ ያደርጋልም ተብሏል።

ከዚህም ሌላ ዳኞች በጉባኤው ስለሚኖራቸው አባልነት ሁኔታና ስብጥር እንዲሁም የአገልግሎት ጊዜና ስንብት በማሻሻያው ትኩረት ተደርጎበታል።

የዳኞች የዳኝነት የጡረታ ጊዜ በወንጀል ያለመከሰስ መብት በበቂ ጥናት ምርምር በረቂቁ ተካቷል።

አዲሱ አዋጅ ዳኞች የፖለቲካ ፓርቲዎች አባል ወይም የፖለቲካ ተሳታፊ እንዳይሆኑ ይከለክላል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም