ሴቶች በተለያዩ መስኮች በመሳተፍ ብቃት እንዳላቸው ማሳየት ይጠበቅባቸዋል ተባለ

384

አዲሰ አበባ  መጋቢት 13/2011 የኢትዮጵያ ሴቶች ወደ አመራርነት ለመምጣት “የይቻላል መንፈስንና እውቀትን ማዳበር” እንደሚያስፈልጋቸው በከፍተኛ የስራ ኃላፊነት የሚያገለግሉ ሴቶች ገለጹ።

በኢትዮጵያ የሴቶችን ምጣኔ ኃብታዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በተለይ ካለፉተ ሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ የተለያዩ ህጎችን ከማውጣት አንስቶ ዘርፈ በዙ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው።

በዚህም አመራሮችን ወደፊት ከማምጣትና ተጠቃሚነታቸውን ከማጉላት አንጻር መልካም ጅምሮች እየታዩ መሆናቸውም ይነገራል።

ሆኖም አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሴቶችን የአመራር ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን በተመለከተ በአሁኑ ወቅት የሚታየው ለውጥ በሚፈለገው መጠን እያደገ አይደለም።

እናም የሚታየው መጠነኛ መሻሻል በስፋት ይቀጥል ዘንድ ” የይቻላል መንፈስን” መላበስ እንደሚገባቸው በተለያዩ ድርጅቶች የስራ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ ሴቶች ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

በህይወት አጋጣሚ በርካታ ፈተናዎች ይገጥማሉ የሚሉት ሀሳብ ሰጪዎቹ  ሴቶች ፈተናዎቹን በመቋቋምና የእውቀት አድማሳቸውን በማስፋት አስቸጋሪ የሆኑ ሁኔታዎችን ማለፍ ይቻላሉ ይላሉ።

ይህንን ብቃት በማዳበር ለአገርና ለህዝብ ሊያበረክቱ የሚችሉትን አስተዋጽኦ ማሳየት እንዳለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ራሳቸውን ለማሳደግና ለማጎልበት ከመንግስት የሚሰጡ ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ያስገነዘቡት አስተያየት ሰጪዎቹ የተለያየ ሴቶች በራሳቸው በመጣርም ራሳቸውን ማብቃት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

ወይዘሮ ትህትና ሙሉሸዋ የዋሪት ሙሉ ጥላ ማኔጂንግ ዳሬክተር አመራር ውስጥ ለመግባት እውቀትና ጥረት ወሳኝ እንደሆነ ተናግረው እችላለው በሚል መንፈስ ተስፋ ባለመቆረጥ ያሰቡበት ደረጃ መድረስ ይቻላል ብለዋል፡፡

ወይዘሮ አዳነች ከበደ በኤውብ ድርጅት ውስጥ የቦርድ አባል በበኩላቸው ሴቶች በአሁኑ ወቅት ወደ አመራርነት እየመጡ እንደሆነ እድሉን ካገኙ እንደሚችሉ ተናገረው ሴቶች የበለጠ ብቁ ሆነው እንዲገኙ በትሬኒንግ ማገዝ ይገባል ብለዋል፡፡

ቤተሰብ በልጅነት የሰጣቸው የራስ መተማመናቸውን እንዳሳደገላቸው ውጤታማነት ከልጅነት ጀምሮ በራስ መተማመናቸው እንዳሳደገላቸው በመናገር የወላጅ አስተዳደግ ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት ወይዘሪት መቲ ሸዋዬ ይልማ በ2018 የኤውብ የግል ድርጅት ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡

ሴቶች በአመራር ቦርዶች ውሰጥ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲጎለብት አስገዳጅ ህግ ስራ ላይ እንዲውል ከተደረገባቸው የአውሮፓ አገራት መካከል ፈረንሳይ፣ ኖርዌይና ስዊዲን ይጠቀሳሉ።

በአፍሪካ ደግሞ በአመራር ቦርዶች ውስጥ የሴቶችን ድርሻ በማሳደግ ኬኒያ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚ ናቸው።