ባየርን ሙኒክ በኢትዮጵያ የስፖርት ስልጠና ማዕከል እንዲከፍት ተጠየቀ

76

አዲስ አበባ መጋቢት 13/2011 የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ በኢትዮጵያ የስፖርት ስልጠና ማዕከል መክፈት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽ አስታውቋል፡፡

የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እርስቱ ይርዳ ከጀርመን አምባሳዳር ቢሪታ ዋገኔር ጋር በተወያዩበት ወቅት የባየርን ሙኒክ ክለብ በኢትዮጵያ የስፖርት ስልጠና ማዕከል መክፈት በሚችልበት ሁኔታ ላይ መነገጋገራቸውን ነው ኮሚሽኑ የገለጸው።

ኮሚሽነሩ አቶ እርስቱ ይርዳ በውይይታቸው ወቅት ጀርመን በኢትዮጵያ የልማት ስራዎች ላይ የምታደርገው ድጋፍ በስፖርቱም ተግባራዊ እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ቢሪታ ዋገኔር  በበኩላቸው ጀርመን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በማንኛውም የልማት መስክ ላይ በትብብር እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።

በስፖርቱ መስክ ወደ ስራ መግባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተዘጋጅቶ በሚቀጥለው ሚያዝያ ከጀርመን ሀገር ከሚመጡ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊና የስፖርት ክለብ ባለሙያዎች እና ከስፖርት ኮሚሽን ጋር ለመፈራረም እንደታሰበም ነው የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም