የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከማሊ አቻው 1ለ1 ተለያየ

57

አዲስ አበባ መጋቢት 12/2011 የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከማሊ አቻው ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረገው ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያየ።

በተደረገው ጨዋታ የእንግዳው ቡድን በ 52 ኛው ደቂቃ በሳማዲያሪ ዲያንካ አማካኝነት ባስቆጠረው ግብ እስከ 73 ኛው ደቂቃ መምራት ቢችልም የኢትዮጵያ ቡድን በተከላካዩ ደስታ ደሙ አማካኝነት በ74 ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ አቻ ሆነዋል።

በጨዋታው የኢትዮጵያ ቡድን ተደጋጋሚ የግብ እድሎችን ቢፈጥርም በአጨራረስ ድክመት ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር አልቻለም።

ቡድኑ በመልሱ ጨዋታ የአጨራረስ ድክመቱን አርሞ ማጣሪያውን ለማለፍ መጫወት ይጠበቅበታል።

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ መጋቢት 17 በማሊ ዋና ከተማ ባማኮ እንደሚደረግ መርሃ ግበር ወጥቶለታል።

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን የማሊ አቻውን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ  በቀጣዩ ዙር ማጣሪያ ከሩዋንዳ፣ ሞሮኮና ዴሞክራቲክ ኮንጎ አንዳቸውን የሚያገኝ ይሆናል።

ጨዋታው በጃፓን ቶኪዮ እ.አ.አ በ2020 ለሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ እግር ኳስ ውድድር ለመሳተፍ  የተደረገ የማጣሪያ ግጥሚያ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም