በምእራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

99

መጋቢት 10/2011 በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ ሁምና ዋቃዮ ቀበሌ በታጣቂ ሃይሎች በደረሰ ጥቃት የአምስት ሰዎች ህይወት  ማለፉ ተገልጿል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ  መረጃ እንደሚያመለክተው  ጥቃቱ የደረሰው  ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ላይ  ነበር።

የጦር መሳሪያ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጥቃቱን እንዳደረሱትም ነው ቢሮው ያስታወቀው።

በጥቃቱ  ህይወታቸው ካለፈው አምስት ሰዎች ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ የውጭ ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል።

ስለ ጥቃቱ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚያቀርብም ቢሮው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም