በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን ሽኝት ተደረገላቸው

86

አዲስ አበባ መጋቢት 8/2011 ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን ሽኝት ተደረገላቸው።

በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይም የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባ ዱላ ገመዳና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

ቀደም ሲልም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ የበረራ ሰራተኞችና መንገደኞች በአየር መንገዱ ቅጥር ግቢ የመታሰቢያ ዝግጅት አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም የአደጋውን መንስኤ ለማጣራትም ለምርመራ ወደ ፈረንሳይ ያቀናው የአውሮፕላኑ የመረጃ ሣጥን (ብላክ ቦክስ) ምርመራ ተጀምሯል።

በአውሮፕላኑ አደጋ 18 ኢትዮጵያዊንን ጨምሮ 157 የ35 አገራት ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም