ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል በጌዲኦ ዞን የተጠለሉ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነው

70

ሀዋሳ መጋቢት 6/2011 የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል ከአጎራባች አካባቢ ተፈናቅለው  በጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ ተጠልለው የሚገኙ ዜጎችን  እየጎበኙ ነው፡፡

ሚኒስትሯ በገደብ ወረዳ ገደብ ስታዲየም  የተጠለሉትን  እነዚህን ተፈናቃዮች  አጽናንተዋል፡፡

መንግስት ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በዚህ ወቅት ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሯ ከተፈናቃይ ተወካዮች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል፡፡

በአሁኑ ወቅት  በገደብ ወረዳ ከ96ሺ በላይ ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም