የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ወድድር በህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ያጠናክራል

79

መቀሌ  መጋቢት 4/2011የዘንድሮው የመላ ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች የስፖርት ወድድር የተወዳዳሪዎችን ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ፤የክልሎች ባህልና እሴቶች መድረክ እንደሚሆን የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ገነት አረፈ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት መቀሌ ከመጋቢት 14- 29/ 2011 የምታስተናግደው ውድድር የተማሪዎችን የእርስ በርስ ግንኙነት በስፖርት ከማሳደግ ባሻገር፤የክልሎችን ባህልና እሴቶች ማስተዋወቂያ መድረክ ይሆናል። 

የአዲስ አበባና ድሬዳዋ አስተዳደሮችን ጨምሮ የዘጠኙ ክልሎች ተማሪዎች በሚሳተፉበት መድረክ  የክልሎች ወግ፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ አለባበስ፣ ምርትና አመጋገብ ይተዋወቁበታል ብለዋል፡፡

በአግባቡ የመጣበትን ክልል በትክክል ያስተዋወቁም ከዋንጫ እስከ ገንዘብ በሽልማትነት እንደሚሰጠው ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡

የስፖርታዊ ውድድር ዓላማ መሸነፍ ወይም መሸነፍ ሳይሆን፤የፍቅርና አንድነት  ማጠናከር  መሆኑንም አመለክተዋል፡፡

በውድድሩ ከ3ሺህ500 በላይ ተማሪዎች ከ20 ዓይነት በላይ ውድድሮች እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል፡፡

ለውድደሩ ስምንት ሜዳዎች መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም