ሶስተኛው መላው የሴቶች ጨዋታ በጅግጅጋ እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ መጋቢት 4/2011 በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የመላው ሴቶች ጨዋታ ዛሬ 7ኛ ቀኑን ይዟል።

ዛሬን ሳይጨምር በስድስቱ ቀናት ቆይታ በኦሎምፒክ ስፖርቶች፣ በፓራኦሎምፒክ እና መስማት በተሳናቸው ስፖርቶች ኦሮሚያ ክልል በበላይነት  እየመራ ይገኛል።

በኦሎምፒክ ስፖርቶች ኦሮሚያ በ11 ወርቅ 8 ብርና  7 ነሐስ ሜዳሊያ በአንደኝነት ሲቀመጥ አማራ ክልል በ11 ወርቅ 8 ብርና 4 የነሐስ ሜዳሊያ በሁለተኝነት ይከተላል።

ደቡብ ክልል ደግሞ በሁለት ወርቅ፣ 4 ብርና 3 የነሐስ ሜዳሊያ የሶስተኛን ደረጃ ይዟል።

በፓራሊምፒክ ደግሞ ኦሮሚያ 4 ወርቅ 5 ብር 2 የነሐስ ሜዳልያ በማግኘት በአንደኝነት ሲመራ ደቡብ ክልል በ3 ወርቅ 2 ብርና 3 የነሐስ ሜዳሊያ በሁለተኝነት ይከተላል።

አማራ ክልል ደግሞ በ3 ወርቅ በአንድ ብርና 2 የነሐስ ሜዳልያ 3ኛ ደረጃን ይዟል።

መስማት በተሳናቸው ጨዋታዎች ኦሮሚያ፣አዲስ አበባ እና አማራ ክልል እንደ ቅድመ ተከተላቸው ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው እየመሩ ነው።

በዛሬው የ7ኛ ቀን ውሎው በእግር ኳስ ደቡብ ክልል ከአዲስ አበባ የሚጫወቱ ይሆናል።

እንዲሁም ቼዝ፣ መስማት የተሳናቸው የሩጫ ውድድር እና የፓራኦሎምፒክ ውድድሮች ይካሄዳሉ።

የመላ ሴቶች ጨዋታ ውድድር እየተካሄደባቸው ከሚገኙ 10 የስፖርት ዓይነቶች መካከል የአትሌቲክስና የባህል ስፖርቶች ፍፃሜያቸውን አግኝተዋል።

የመላ ሴቶች ጨዋታ ውድድር እስከ መጋቢት 8 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም