ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ ህዝቡ ቅርሶቹን እንዲጠብቅና እንዲንከባከብ አሳሰቡ

471

አዲስ አበባ መጋቢት 4/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ኢትዮጵያዊያን ታሪካዊ ቅርሶቻቸውን የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር የላሊበላ ወቅር አብያተ ክርስቲያናትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ባስተላለፉት መልእክትም ኢትዮጵያዊያን ታሪካዊ ቅርሶቻቸውን የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ ትምህርትና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አደጋ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በቅርቡ በአውሮፓ አገራት ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በላሊበላና ሌሎች ቅርሶች ጥበቃ ዙሪያ መክረው እንደነበር ይታወሳል።

የአሁኑ ጉብኝት ዓላማም የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እየደረሰባቸው ያሉትን ጉዳት በመመልከት የሚጠበቁበትን መንገድ ለመዘየድ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች የተናገሩት። 

ላሊበላ የኢትዮጵያ ታሪክና ማንነት የሚገለፅበት ስፍራ በመሆኑ መላው ዜጋ በራሱ አቅም ሊጠበቀው ይገባል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አስገንዝበዋል።

የላሊበላ ቅርስን መጠበቅ ታሪክን ከማቆየት ባሻገር ወደኢትዮጵያ የሚመጣውን የዓለም ጎብኚ ቁጥር ለማሳደግም ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

ቅርሱን መጠበቅ ይቻል ዘንድ የፈረንሳይ መንግስት ለሚያደርገው ድጋፍም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፕሬዚዳንት ማክሮን ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሳሰቡት ዛሬ ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን በጎበኙበት ወቅት ነው።

የተባበሩት መንግስታት የሳይንስ ፣ ትምህርትና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አደጋ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በቅርቡ በአውሮፓ አገራት ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በላሊበላና ሌሎች ቅርሶች ጥበቃ ዙሪያ መክረው እንደነበር ይታወሳል።

የአሁኑ ጉብኝት ዓላማም የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እየደረሰባቸው ያሉትን ጉዳት በመመልከት የሚጠበቁበትን መንገድ ለመዘየድ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች የተናገሩት። 

ላሊበላ የኢትዮጵያ ታሪክና ማንነት የሚገለፅበት ስፍራ በመሆኑ መላው ዜጋ በራሱ አቅም ሊጠብቀው ይገባል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አስገንዝበዋል።

የላሊበላ ቅርስን መጠበቅ ታሪክን ከማቆየት ባሻገር ወደኢትዮጵያ የሚመጣውን የዓለም ጎብኚ ቁጥር ለማሳደግም ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

ቅርሱን መጠበቅ ይቻል ዘንድ የፈረንሳይ መንግስት ለሚያደርገው ድጋፍም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፕሬዚዳንት ማክሮን ምስጋና አቅርበዋል።