የአየር መንገዱ ሠራተኞች በአደጋው ህይወታቸው ላለፈው የሥራ ባልደረቦቻቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ

53

አዲስ አበባ  መጋቢት 2/2011የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች በአውሮፕላኑ አደጋ ህይወታቸው ላለፈው የሥራ ባልደረቦቻቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ።

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረው ንብረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ቢሾፍቱ አካባቢ መከስከሱ ይታወቃል።

በአደጋውም 149 መንገደኞችንና 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ በረራ ከጀመረ ከስድስት ደቂቃ በኋላ በመከስከሱ በውስጡ የነበሩ 157 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞችም በአደጋው ህይወታቸውን ላጡት የስራ ባልደረቦቻቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልፀዋል።

 ከአየር  መንገዱ ሰራተኖች  መካከል  ካፒቴን የሽዋስ ፈንታሁን  በሰጠው አስተያየት   በባልደረቦቹ  ላይ በደረሰው አደጋ በእጅጉ ማዘኑን ገልጾ  ለሟች ቤተሰቦች  መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

ረዳት አብራሪ ቃሉ ጀማል በበኩሉ አደጋው ከመፈጠሩ ከአንድ ሰአት በፊት ከካፒቴኑ ጋር አብረው እንደነበሩ አስታውሶ  የስራ ባልደረቦቹ  በሞት በመነጠቁ  ማዘኑን  ተናግሯል፡፡

የአውሮፕላኑ አደጋ ትናንት ማለዳ ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተነስቶ በበረራ ላይ እያለ ከስድስት ደቂቃ በኋላ የመከስከስ አደጋ እንደገጠመው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም