ተቋማት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን እየገለፁ ነው

504

አዲስ አበባ መጋቢት 2/2011 የተለያዩ ተቋማት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሀዘን መግለፃቸውን እንደቀጠሉ ነው።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመጽሐፍት ኤጀንሲ በደረሰው አደጋ ሀይወታቸውን ላጡ የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀው ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያዊያ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።

የበረራ ቁጥሩ ኢቲ 302 የሆነው ይህ አውሮፕላን 149 መንገደኞችንና 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ በረራ ከጀመረ ከስድስት ደቂቃ በኋላ በመከስከሱ በውስጡ የነበሩ 157 ሰዎች ህይወት አልፏል።