ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተመድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊን አነጋገሩ

69

አዲስ አበባ መጋቢት 2/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር  ዴቪድ ቤዝሊን ዛሬ  በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና፣ በተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትና በአቅም ግንባታ ዘርፎች ለምታደርጋቸው የልማት እንቅስቃሴዎች የዓለም የምግብ ፕሮግራም የሚሰጠውን ድጋፍ  አጠናክሮ ለመቀጠል ባለው ቁርጠኝነት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል።

የዛሬው ውይይት በጣሊያን ሮም በሁለቱ ባለስልጣናት መካከል ቀደም ሲል የተካሄደው ውይይት አካል እንደሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም