ጎግል በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሀዘኑን ገለፀ

615

አዲስ አበባ መጋቢት 2/2011 ጎግል በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ሳቢያ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች ሀዘኑን ገለፀ።

ትናንት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ተከስክሶ 149 ተሳፋሪዎችና 8 የበረራ ባለሙያዎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል።

በደረሰው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የ33 አገሮች ዜግነት ያላቸው መንገደኞች ህይወት አልፏል።

ይህን ተከትሎ ጎግል በደረሰው አደጋ ሳቢያ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች መታሰቢያ የሚሆን የሃዘን ምልክት በገፁ ላይ አስቀምጧል።

ጎግል በገፁ ላይ የጥቁር ሪባን ምልክት በማስፈር በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች መታሰቢያ አኑሯል።

የበረራ ቁጥሩ ኢቲ 302 የሆነው አውሮፕላን ትላንት ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ ነበር አደጋ የደረሰበት፡፡