ተቋማት በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን እየገለጹ ነው

60

አዲስ አበባ መጋቢት 2/2011 በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።

በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 የበረራ ቁጥር ኢት 302 በደረሰው የመከስከስ አደጋ የሕይወት ሕልፈትና የንብረት መውደም ተቋማቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስትያን፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር የተሰማቸውን ሃዘን ለኢዜአ በላኩት መግለጫ አመልክተዋል።

በዚህ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ለተለያዩ አገራት ዜጎች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉትን ቀሪ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖቹን ላልተወሰነ ጊዜ ከበረራ ውጪ እንዲሆኑ አድርጓል።

በበረራ ወቅት የአውሮፕላኑ የተለያዩ መሣሪያዎች እንቅስቃሴ መዝግቦ የሚያስቀረውን (DFDR) ወይም የመረጃ ሳጥን (balck box) አደጋው በደረሠበት ቦታ ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም