የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ የውጭ አገር ዜጎች ለአምባሳደሮቻቸው ገለጻ ያደርጋል

76

አዲስ አበባ መጋቢት 2/2011 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ የውጭ አገር ዜጎች ለአምባሳደሮቻቸው ገለጻ ሊያደርግ ነው።

ትናንት ከአዲስ አበባ  ኬኒያ ናይሮቢ ሲጓዝ  የተከሰከሰው የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የ33 አገራት 149 መንገደኞችና ስምንት የበረራ አስተናጋጆችን ይዞ እንደነበር ይታወቃል።

ከተሳፋሪዎቹ መካከል 32ቱ ኬኒያውያን ሲሆኑ፤ 17ቱ ኢትዮጵያዊያን ቀሪዎቹ ደግሞ የሌሎች አገራት ዜጎች ናቸው።

አደጋው የደረሰበት ትናንት ማለዳ ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በተነሳ በስድስት ደቂቃ ልዩነት መሆኑን የተገለጸ ሲሆን የአደጋው መንስኤ እስካሁን አልታወቀም።

ስለ አደጋው መረጃ ይሰጣል ተብሎ የሚታሰበው የመረጃ ሳጥን (ብላክ ቦክስ) ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም