የኤርትራ መንግስት በአውሮፕላን መከስከስ አደጋው የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

73

አዲስ አበባ መጋቢት 1/2011 የኤርትራ መንግስት ሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወታቸውን ባጡበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ማዘኑን ገለጸ።

ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ ኬኒያ ሲጓዝ በምስራቅ ሸዋ ጊምቢቹ አካባቢ የተከሰከሰው የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የ33 አገራት ዜግነት ያላቸው 149 መንገደኞችና ስምንት የበረራ ሰራተኞችን የያዘ ነበር።

ከተሳፋሪዎቹ መካከል 32ቱ ኬኒያዊያን ሲሆኑ፤ 17ቱ ኢትዮጵያዊያን ቀሪዎቹ ደግሞ የሌሎች አገራት ዜጎች ሲሆኑ በአደጋው ሁሉም ህይወታቸውን አጥተዋል።

የኤርትራ መንግስት በአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ በኩል ለኢትዮጵያ ባስተላለፈው መልዕክት በአደጋው የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

በአገሪቱ መንግስትና ህዝብ ስምም ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም